ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዮሐንስ 6:17-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በጀልባውም ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም ለመሻገር ተነሡ። ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ወደ እነርሱ ገና አልመጣም ነበር።

18. ኀይለኛ ነፋስ ይነፍስ ስለ ነበር ባሕሩ ተናወጠ።

19. አምስት ወይም ስድስት ኪሎ ሜትር ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በውሃ ላይ እየተራመደ ወደ ጀልባዋ ሲመጣ አይተው ደነገጡ።

20. እርሱ ግን፣ “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ” አላቸው።

21. እነርሱም እንዲሳፈር ፈለጉ፤ ጀልባዋም ወዲያውኑ ወደሚሄዱበት ዳርቻ ደረሰች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዮሐንስ 6