ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዮሐንስ 16:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ይህን በመናገሬም ልባችሁ በሐዘን ተሞልቶአል፤

7. ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መሄዴ ይበጃችኋል። እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድሁ ግን እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፤

8. በሚመጣበትም ጊዜ ዓለምን ስለ ኀጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ይወቅሳል።

9. ስለ ኀጢአት ሲባል፣ ሰዎች በእኔ ስለማያምኑ ነው፤

10. ስለ ጽድቅ፣ ወደ አብ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ ነው፤

11. ስለ ፍርድም፣ የዚህ ዓለም ገዥ ስለ ተፈረደበት ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዮሐንስ 16