ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዮሐንስ 1:36-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

36. ኢየሱስንም በዚያ ሲያልፍ አይቶ፣ “እነሆ! የእግዚአብሔር በግ” አለ።

37. ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ይህን ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት።

38. ኢየሱስም ዘወር ብሎ ሲከተሉት አየና፣ “ምን ትፈልጋላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው።እነርሱም፣ “ረቢ፣ የት ትኖራለህ?” አሉት፤ ‘ረቢ’ ማለት መምህር ማለት ነው።

39. እርሱም፣ “ኑና እዩ” አላቸው።ስለዚህ ሄደው የት እንደሚኖር አዩ፤ በዚያም ዕለት አብረውት ዋሉ፤ ከቀኑም ዐሥር ሰዓት ያህል ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዮሐንስ 1