ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 3:4-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እያንዳንዱ ቤት የራሱ ሠሪ አለው፤ ነገር ግን ሁሉን የሠራ እግዚአብሔር ነው።

5. ሙሴ ወደ ፊት ስለሚነገረው ነገር እየመሰከረ፣ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ እንደ አንድ ታማኝ አገልጋይ ነበር፤

6. ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ላይ እንደ ታማኝ ልጅ ነው። እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።

7. ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚል፣“ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

8. በምድረ በዳ በፈተና ቀን፣በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ልባችሁን አታደንድኑ።

9. አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።

10. በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤እንዲህም አልሁ፤ ‘ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል፤መንገዴንም አላወቁም፤’

11. ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤“ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።”

12. ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 3