ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 3:15-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ይኸውም፣“ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ፣በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው።

16. ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብፅ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?

17. አርባ ዓመት የተቈጣውስ እነማንን ነበር? ኀጢአት ሠርተው ሬሳቸው በምድረ በዳ ወድቆ የቀረውን አይደለምን?

18. ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ?

19. እንግዲህ ሊገቡ ያልቻሉት ካለማመናቸው የተነሣ እንደሆነ እንረዳለን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 3