ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 12:4-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ከኀጢአት ጋር ስትታገሉ ገና ደማችሁን እስከ ማፍሰስ ድረስ አልተቃወማችሁም።

5. ልጆች እንደመሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦“ልጄ ሆይ፤ የጌታን ቅጣት አታቃል፤በሚገሥጽህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤

6. ምክንያቱም ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፤እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል።”

7. እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ ይዞአችኋልና የተግሣጽን ምክር ታገሡ፤ ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?

8. ልጆች ሁሉ በሚቀጡበት ቅጣት ተካፋይ ካልሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 12