ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 11:37-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተወግተው ሞቱ፤ እየተጐሳቈሉ፣ እየተሰደዱና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ቈዳ ለብሰው ዞሩ፤

38. ዓለም ለእነርሱ አልተገባቻቸውምና። በየበረሓውና በየተራራው፣ በየዋሻውና በየጒድጓዱ ተንከራተቱ።

39. እነዚህ ሁሉ ስለ እምነታቸው የተመሰከረላቸው ቢሆኑም ከእነርሱ ማንም የተስፋውን ቃል የተቀበለ የለም።

40. እግዚአብሔር ለእኛ የሚበልጥ ነገር ስላዘጋጀ፣ ያለ እኛ ፍጹማን ሊሆኑ አልቻሉም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 11