ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕብራውያን 1:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤

12. እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”

13. እግዚአብሔር፣“ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?

14. መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕብራውያን 1