ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤፌሶን 4:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንሁ እኔ፣ ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።

2. ፍጹም ትሑታንና ገሮች ሁኑ፤ እርስ በርሳችሁም በፍቅር እየተቻቻላችሁ ትዕግሥተኞች ሁኑ።

3. በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ።

4. በተጠራችሁ ጊዜ ወደ አንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ ሁሉ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤

5. አንድ ጌታ፣ አንድ እምነትና አንድ ጥምቀት አለ፤

6. ከሁሉም በላይ የሆነ፣ በሁሉም የሚሠራ፣ በሁሉ የሚኖር የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤፌሶን 4