ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ቲቶ 2:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።

6. እንዲሁም ወጣት ወንዶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።

7. በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስ ተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣

8. የማይነቀፍ ጤናማ አነጋገር አሳይ፤ ይኸውም ተቃዋሚ ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር በማጣት እንዲያፍር ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ቲቶ 2