ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ቲቶ 2:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንተ ግን ከትክክለኛው ትምህርት ጋር ተስማሚ የሆነውን አስተምር።

2. አረጋውያን ጭምቶች፣ የተከበሩ፣ ራሳቸውን የሚገዙና በእምነት፣ በፍቅርና በትዕግሥት ጤናማነት ያላቸው እንዲሆኑ ምከራቸው።

3. እንዲሁም አሮጊቶች በአኗኗራቸው የተከበሩ እንዲሆኑ፣ በጎ የሆነውን የሚያስተምሩ እንጂ የሰው ስም የሚያጠፉ ወይም በወይን ጠጅ ሱስ የተጠመዱ እንዳይሆኑ አስተምራቸው፤

4. እንዲህ ከሆኑ፣ ወጣት ሴቶች ባሎቻቸውንና ልጆቻቸውን እንዲወዱ ማስተማር ይችላሉ፤

5. የእግዚአብሔር ቃል በማንም ዘንድ እንዳይሰደብ ራሳቸውን የሚገዙና ንጹሓን፣ በቤት ውስጥ በሥራ የተጠመዱ፣ ቸሮች፣ ለባሎቻቸው የሚገዙ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው።

6. እንዲሁም ወጣት ወንዶች ራሳቸውን እንዲገዙ ምከራቸው።

7. በማንኛውም ነገር መልካም የሆነውን ነገር በማድረግ ራስህን አርኣያ አድርገህ አቅርብላቸው። በምታስ ተምራቸውም ትምህርት ጭምተኛነትን፣ ቁም ነገረኛነትን፣

8. የማይነቀፍ ጤናማ አነጋገር አሳይ፤ ይኸውም ተቃዋሚ ስለ እኛ የሚናገረውን መጥፎ ነገር በማጣት እንዲያፍር ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ቲቶ 2