ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ቈላስይስ 4:14-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የተወደደው ሐኪሙ ሉቃስ እንዲሁም ዴማስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።

15. በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች፣ ለንምፉን፣ በቤቷም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ።

16. ይህች መልእክት ከተነበበችላችሁ በኋላ በሎዶቅያ ላለችው ቤተ ክርስቲያን ደግሞ እንድትነበብ አድርጉ፤ እናንተም ደግሞ በሎዶቅያ ያለችውን መልእክት አንብቡ።

17. ለአክሪጳም፣ “በጌታ የተቀበልኸውን አገልግሎት ከፍጻሜ ለማድረስ ተጠንቀቅ” በሉልኝ።

18. ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ቈላስይስ 4