ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሮሜ 16:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በክንክራኦስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እኅታችንን ፌቤንን ዐደራ እላችኋለሁ።

2. ለቅዱሳን ተገቢ በሆነው አቀባበል በጌታ እንድትቀበሏትና ከእናንተም የምትፈልገውን ማንኛውንም ርዳታ እንድታደርጉላት አሳስባችኋለሁ፤ ለብዙ ሰዎችና ለእኔም ጭምር ታላቅ ድጋፍ ነበረችና።

3. በክርስቶስ ኢየሱስ አብረውኝ ለሚያገለግሉት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ።

4. እነርሱም ለእኔ ሲሉ ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ሰጡ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን የአሕዛብ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያመሰግኗቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሮሜ 16