ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ራእይ 4:8-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች ነበሯቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸው በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ፤ ቀንና ሌሊትም፦“ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፤ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ”ማለትን አያቋርጡም።

9. ሕያዋን ፍጡራኑ በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ክብር፣ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፣

10. ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ሕያው ሆኖ ለሚኖረው ይሰግዱ ነበር፤ አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው እንዲህ ይላሉ፤

11. “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ሆነዋልምና።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ራእይ 4