ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ራእይ 2:22-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. ስለዚህ በመከራ ዐልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ ከእርሷም ጋር የሚያመነዝሩትን፣ ከመንገዷ ንስሓ ካልገቡ፣ ብርቱ ሥቃይ አመጣባቸዋለሁ፤

23. ልጆቿንም በሞት እቀጣቸዋለሁ፤ ከዚያም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ ልብንና ሐሳብን የምመረምር መሆኔን ይረዳሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላችኋለሁ።

24. ትምህርቷን ላልተከተላችሁና የሰይጣንም ጥልቅ ምስጢር ነው የሚባለውን ላልተቀበላችሁ፣ በትያጥሮን ለቀራችሁት ለእናንተ ግን ይህን እላለሁ፤ በእናንተ ላይ ተጨማሪ ሸክም አልጭንባችሁም፤

25. ብቻ እኔ እስክመጣ ድረስ ያላችሁን አጥብቃችሁ ያዙ።

26. ድል ለሚነሣና ሥራዬንም እስከ መጨረሻው ለሚፈጽም በአሕዛብ ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ፤ እርሱም፦

27. ‘በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላ ዕቃም ይፈጫቸዋል፤ ይህም ልክ እኔ ከአባቴ ዘንድ ሥልጣንን እንደ ተቀበልሁ ነው፤

28. እኔም የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ።

29. መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ራእይ 2