ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ራእይ 2:14-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤ የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው መሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን ያስተማረውን የበለዓምን ትምህርት የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ፤

15. የኒቆላውያንን ትምህርት የሚከተሉ ሰዎችም በአንተ ዘንድ አሉ።

16. ስለዚህ ንስሓ ግባ፤ አለዚያ ቶሎ እመጣብሃለሁ፤ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።

17. መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ፤ ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈበት ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።

18. “በትያጥሮን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ እንደ እሳት ነበልባል የሆኑ ዐይኖችና በእሳት ቀልጦ የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል፤

19. ሥራህን፣ ፍቅርህን፣ እምነትህን፣ አገልግሎትህንና ትዕግሥትህን ዐውቃለሁ፤ ደግሞም ከመጀመሪያው ሥራህ ይልቅ የአሁኑ እንደሚበልጥ ዐውቃለሁ።

20. ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ነቢይ ነኝ የምትለዋን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል፤ እርሷ አገልጋዮቼ እንዲሴ ስኑና ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉ በትምህርቷ ታስታቸዋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ራእይ 2