ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ራእይ 18:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም ነጸብራቅ የተነሣ ምድር በራች፤

2. እርሱም በብርቱ ድምፅ እንዲህ ብሎ ጮኸ፤“ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!የአጋንንት መኖሪያ፣የርኩሳን መናፍስት ሁሉ መጠጊያ፣የርኩስና የአስጸያፊ ወፎች ሁሉ መጠለያ ሆነች።

3. ሕዝቦች ሁሉ የዝሙቷን ቍጣ ወይን ጠጅ ጠጥተዋልና፤የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረዋል፤የምድርም ነጋዴዎች ከብዙ ምቾቷ ኀይልየተነሣ በልጽገዋል።”

4. ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤“ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፣ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፣ከእርሷ ውጡ፤

5. ኀጢአቷ እስከ ሰማይ ድረስ ተከምሮአልና፤እግዚአብሔርም ዐመፃዋን አስታውሶአል።

6. በሰጠችው መጠን ብድራቷን መልሱላት፤ለሠራችው ሁሉ ዕጥፍ ክፈሏት፤በቀላቀለችውም ጽዋ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ራእይ 18