የእግዚአብሔር ባሪያ የሆነውን የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር፤“ሁሉን ቻይ ጌታ አምላክ ሆይ፤ሥራህ ታላቅና አስደናቂ ነው።የዘመናት ንጉሥ ሆይ፤መንገድህ ጽድቅና እውነት ነው።