ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 3:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ዙሪያ ካለው አገር ሁሉ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይጐርፉ፣

6. ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።

7. ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የእፉኝት ልጆች! ለመሆኑ ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ

8. ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤

9. ‘አብርሃም አባት አለን’ በማለት ራሳችሁን አታታሉ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣ ይችላል እላችኋለሁና።

10. እነሆ፤ ምሣር የዛፎችን ሥር ሊቈርጥ ተዘጋጅቶአል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል።

11. “እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ጫማውን መሸከም የማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበልጥ ኀያል ከእኔ በኋላ ይመጣል። እርሱም በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማቴዎስ 3