ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 3:1-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በዚያን ወራት መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ እየሰበከ መጣ።

2. ስብከቱም፣ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሓ ግቡ” የሚል ነበር።

3. በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረለት እርሱ ነው፤“በምድረ በዳ፣‘የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ጎዳናውንም አስተካክሉ’ እያለ የሚጮህ ድምፅ።”

4. የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር። ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበር።

5. ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ዙሪያ ካለው አገር ሁሉ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ይጐርፉ፣

6. ኀጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።

7. ብዙ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያን ወደሚያጠምቅበት ስፍራ ሲመጡ ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “እናንት የእፉኝት ልጆች! ለመሆኑ ከሚመጣው ቍጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ

8. ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤

9. ‘አብርሃም አባት አለን’ በማለት ራሳችሁን አታታሉ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣ ይችላል እላችኋለሁና።

10. እነሆ፤ ምሣር የዛፎችን ሥር ሊቈርጥ ተዘጋጅቶአል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማቴዎስ 3