ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 22:38-46 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. ይህ የመጀመሪያውና ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ ነው፤

39. ሁለተኛውም ያንኑ ይመስላል፤ ይህም፣ ‘ጎረቤትህን እንደ ራስህ ውደድ’ የሚለው ነው፤

40. ሕግና ነቢያት በሙሉ በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ የተንጠለጠሉ ናቸው።”

41. ፈሪሳውያን ተሰብስበው ሳሉ ኢየሱስ፣ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፤

42. “ስለ ክርስቶስ ምን ይመስላችኋል? የማንስ ልጅ ነው?”እነርሱም፣ “የዳዊት ልጅ ነው” አሉት።

43. እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ታዲያ፣ ዳዊት በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ለምን ‘ጌታዬ’ ይለዋል? ለምንስ፣ እንዲህ ይለዋል?

44. “ ‘እግዚአብሔር ጌታዬን፤ ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካንበረክ ክልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ።” ’

45. ስለዚህ ዳዊት፣ ‘ጌታዬ’ ብሎ ከጠራው፣ እንዴት ልጁ ሊሆን ይችላል?”

46. አንድ ቃል ሊመልስለት የቻለ ወይም ከዚያን ቀን ጀምሮ ሊጠይቀው የደፈረ ማንም አልነበረም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማቴዎስ 22