ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 2:2-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” ሲሉ ጠየቁ።

3. ንጉሡ ሄሮድስ ይህን በሰማ ጊዜ ታወከ፤ እንዲሁም መላዪቱ ኢየሩሳሌም አብራ ታወከች።

4. እርሱም የካህናት አለቆችንና የአይሁድ ሃይማኖት መምህራንን በሙሉ ሰብስቦ፣ ክርስቶስ የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው።

5. እነርሱም፣ “በይሁዳ ቤተ ልሔም፤ ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፎአልና አሉ፤

6. “ ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተ ልሔም፣ከሌሎቹ የይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፤የሕዝቤ የእስራኤል ጠባቂ የሚሆን፣ከአንቺ ይወጣልና።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማቴዎስ 2