ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 14:7-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. የምትጠይቀውን ሁሉ ሊሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት።

8. ልጅቷም በእናቷ ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በሳሕን ላይ አድርገህ አሁኑኑ ስጠኝ” አለችው።

9. በዚህ ጊዜ ንጉሡ አዘነ፤ ይሁን እንጂ ስለ መሐላውና ከእርሱ ጋር ስለ ነበሩ እንግዶች ሲል ጥያቄዋ እንዲፈጸምላት አዘዘ።

10. ልኮም በወህኒ ውስጥ እንዳለ የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።

11. የተቈረጠውንም ራስ በሳሕን ላይ አድርገው ለልጅቱ ሰጧት፤ ልጅቱም ወስዳ ለእናቷ ሰጠች።

12. የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትም አስከሬኑን ወስደው ቀበሩት፤ ከዚያም ሄደው የሆነውን ለኢየሱስ ነገሩት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማቴዎስ 14