ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 14:33-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

33. ከዚያም በጀልባው ውስጥ የነበሩት፣ “በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።

34. ባሕሩን ከተሻገሩ በኋላ ጌንሴሬጥ ወደተባለ ቦታ ደረሱ።

35. ነዋሪዎቹም ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በዙሪያው ወዳለ አካባቢ ሁሉ መልእክት ላኩ፤ የታመሙትን ሁሉ ወደ እርሱ በማስመጣት፣

36. በሽተኞቹ የልብሱን ጫፍ ብቻ ይነኩ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት፤ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማቴዎስ 14