ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22
  23. 23
  24. 24
  25. 25
  26. 26
  27. 27
  28. 28

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማቴዎስ 1 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የኢየሱስ የትውልድ ሐረግ

1. የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው፤

2. አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ይስሐቅ ያዕቆብን ወለደ፤ያዕቆብ ይሁዳንና ወንድሞቹን ወለደ፤

3. ይሁዳ ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ፋሬስ ኤስሮምን ወለደ፤ኤስሮምም አራምን ወለደ፤

4. አራም አሚናዳብን ወለደ፤አሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤

5. ሰልሞን ቦዔዝን ከረዓብ ወለደ፤ቦዔዝ ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ኢዮቤድ እሴይን ወለደ፤

6. እሴይ ንጉሥ ዳዊትን ወለደ።ዳዊት የኦርዮ ሚስት ከነበረችውሰሎሞንን ወለደ፤

7. ሰሎሞን ሮብዓምን ወለደ፤ሮብዓም አቢያን ወለደ፤አቢያም አሣፍን ወለደ፤

8. አሣፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ኢዮሣፍጥ ኢዮሆራምን ወለደ፤ኢዮሆራም ዖዝያንን ወለደ፤

9. ዖዝያን ኢዮአታምን ወለደ፤ኢዮአታም አካዝን ወለደ፤አካዝ ሕዝቅያስን ወለደ፤

10. ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ምናሴ አሞንን ወለደ፤አሞንም ኢዮስያስን ወለደ፤

11. ኢዮስያስ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ፣ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ፤

12. ከባቢሎን ምርኮ በኋላ፣ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤

13. ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ኤልያቄም አዛርን ወለደ፤

14. አዛር ሳዶቅን ወለደ፤ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤

15. ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ማታን ያዕቆብን ወለደ፤

16. ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ዮሴፍም የኢየሱስ ክርስቶስ እናትየማርያም እጮኛ ነበር።

17. እንግዲህ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ልደት ዐሥራ አራት ትውልድ ይሆናል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት

18. የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነው፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳይገናኙ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች።

19. እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ።

20. በዚህ ሐሳብ ሳለ፣ የጌታ መልአክ በሕልም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፤ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፤ እጮኛህን ማርያምን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ፤ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና።

21. ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።”

22. ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤

23. “እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው።

24. ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቃ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ እንዳዘዘው ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት።

25. ይሁን እንጂ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ የተወለደውንም ሕፃን፣ “ኢየሱስ” ብሎ ጠራው።