ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 8:10-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ዳልማኑታ ወደተባለ ስፍራ ሄደ።

11. ፈሪሳውያንም ወጥተው ከኢየሱስ ጋር ይከራከሩ ጀመር። ሊፈትኑትም ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።

12. እርሱም በመንፈሱ እጅግ በመቃተት፣ “ይህ ትውልድ ምልክት የሚፈልገው ለምንድን ነው? እውነት እላችኋለሁ፤ ለዚህ ትውልድ ምንም ምልክት አይሰጠውም!” አለ።

13. ከዚያም ትቶአቸው በጀልባ ወደ ማዶ ተሻገረ።

14. ደቀ መዛሙርቱ እንጀራ መያዝ ስለ ረሱ፣ ከአንድ እንጀራ በቀር በጀልባ ውስጥ ምንም አልነበራቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማርቆስ 8