ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 2:24-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ፈሪሳውያንም፣ “እነሆ፤ በሰንበት ቀን ለምን የተከለከለ ነገር ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት።

25. እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ዳዊት በተራበና የምግብ ፍላጎት በጸናበት ጊዜ አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር ያደረገውን አላነበባችሁምን?

26. በሊቀ ካህናቱ በአብያታር ዘመን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ካህናት ብቻ እንዲበሉት የተፈቀደውን የተቀደሰ ኅብስት ራሱ በልቶ አብረውት ለነበሩትም ሰዎች ሰጣቸው።”

27. ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ሰንበት ለሰው ተፈጠረ እንጂ፣ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፤

28. ስለዚህ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታዋ ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማርቆስ 2