ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 2:20-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወቅት ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ግን ይጾማሉ።

21. “በአሮጌ ልብስ ላይ አዲስ ጨርቅ የሚጥፍ ማንም የለም፤ ይህ ቢደረግ ግን፣ አዲሱ ጨርቅ አሮጌውን ይቦጭቀዋል፤ ቀዳዳውም የባሰ ይሰፋል።

22. እንዲሁም አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ የሚያስቀምጥ የለም፤ ይህ ከተደረገማ የወይን ጠጁ አቍማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም አቍማዳውም ይበላሻሉ። ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ መቀመጥ ያለበት በአዲስ አቍማዳ ነው።”

23. በሰንበት ቀን ኢየሱስ በእርሻ መካከል ሲያልፍ፣ አብረውት በመጓዝ ላይ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እሸት ይቀጥፉ ጀመር።

24. ፈሪሳውያንም፣ “እነሆ፤ በሰንበት ቀን ለምን የተከለከለ ነገር ያደርጋሉ?” ሲሉ ጠየቁት።

25. እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ዳዊት በተራበና የምግብ ፍላጎት በጸናበት ጊዜ አብረውት ከነበሩት ሰዎች ጋር ያደረገውን አላነበባችሁምን?

26. በሊቀ ካህናቱ በአብያታር ዘመን ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ካህናት ብቻ እንዲበሉት የተፈቀደውን የተቀደሰ ኅብስት ራሱ በልቶ አብረውት ለነበሩትም ሰዎች ሰጣቸው።”

27. ደግሞም እንዲህ አላቸው፤ “ሰንበት ለሰው ተፈጠረ እንጂ፣ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፤

28. ስለዚህ የሰው ልጅ የሰንበት ጌታዋ ነው።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማርቆስ 2