ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማርቆስ 14:61-64 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

61. ኢየሱስ ግን ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም።ሊቀ ካህናቱም እንደ ገና፣ የቡሩኩ ልጅ፣ ክርስቶስ አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው።

62. ኢየሱስም፣ “አዎን ነኝ፤ የሰው ልጅ በኀያሉ ቀኝ ሲቀመጥ፣ በሰማይ ደመናም ሲመጣ ታዩታላችሁ” አለ።

63. ሊቀ ካህናቱም ልብሱን ቀደደና፣ እንዲህ አለ፤ “ሌላ ምን ምስክር ያስፈልገናል?

64. ስድቡን ሰምታችኋል፤ ታዲያ፣ ምን ይመስላችኋል?”፤እነርሱም ሞት ይገባዋል በማለት በአንድ ቃል ፈረዱበት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማርቆስ 14