ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 8:37-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ መጠመቅ ትችላለህ” አለው። ጃንደረባውም፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ አምናለሁ” ሲል መለሰለት፤

38. ሠረገላውም እንዲቆም አዘዘ። ከዚያም ሁለቱ አብረው ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም ጃንደረባውን አጠመቀው።

39. ከውሃውም በወጡ ጊዜ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ነጥቆ ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚህ በኋላ አላየውም፤ ሆኖም ደስ እያለውም ጒዞውን ቀጠለ።

40. ከዚያ በኋላ ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ፤ ቂሳሪያም እስኪደርስ ድረስ፣ በሚያልፍባቸው ከተሞች ሁሉ ወንጌልን ይሰብክ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 8