ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 7:49-53 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

49. “ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ታዲያ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ?ይላል ጌታ፤ወይንስ ማረፊያ የሚሆነኝ የትኛው ቦታ ነው?

50. ይህን ሁሉ የሠራው እጄ አይደለምን?’

51. “እናንት ልባችሁና ጆሮአችሁ ያልተገረዘ፣ አንገተ ደንዳኖች ልክ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ሁል ጊዜ ትቃወማላችሁ።

52. ከነቢያት መካከል አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን አለ? የጻድቁን መምጣት አስቀድመው የተናገሩትን እንኳ ገድለዋል፤ እናንተም አሁን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት፤ ገደላችሁትም፤

53. በመላእክት አማካይነት የተሰጣችሁንም ሕግ ተቀበላችሁ እንጂ አልጠበቃችሁትም።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 7