ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 3:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ ይኸውም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት፣ ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር።

2. ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት እንዲለምን፣ ሰዎች በየዕለቱ ተሸክመው ‘ውብ’ በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ የሚያስቀምጡት አንድ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበረ፤

3. እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ አይቶ ምጽዋት ለመናቸው።

4. ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋር ወደ እርሱ ትኵር ብሎ አየውና፣ “እስቲ ወደ እኛ ተመልከት” አለው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 3