ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 24:8-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እንግዲህ አንተ ራስህ መርምረኸው እርሱን የከሰስንበትን ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን ልታረጋግጥ ትችላለህ።”

9. አይሁድም ነገሩን እንደ ተባለው መሆኑን በመደገፍ በክሱ ተባበሩ።

10. አገረ ገዡም እንዲናገር በእጁ ምልክት በሰጠው ጊዜ፣ ጳውሎስ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ ፈራጅ መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ የመከላከያ መልሴን የማቀርበው በደስታ ነው።

11. ልሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም የመጣሁት ከዐሥራ ሁለት ቀን በፊት መሆኑን አንተው ራስህ በቀላሉ ማረጋገጥ ትችላለህ።

12. ከሳሾቼም በቤተ መቅደስ ከማንም ጋር ስከራ ከር ወይም በምኵራብ ወይም በከተማ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ሕዝብን ሳነሣሣ አላገኙኝም።

13. አሁንም ለተከሰስሁበት ነገር ማስረጃ ሊያቀርቡልህ አይችሉም።

14. ይሁን እንጂ፣ እነርሱ ኑፋቄ በሚሉት በጌታ መንገድ የአባቶቻችንን አምላክ አመልካለሁ፤ በሕጉ የታዘዘውንና በነቢያት የተጻፈውን ሁሉ አምናለሁ፤

15. ደግሞም እንደነዚህ ሰዎች ሁሉ፣ ጻድቃንና ኀጥአን ከሙታን እንደሚነሡ በእግዚአብሔር ተስፋ አለኝ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 24