ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 24:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ከዚያም ለጳውሎስ መጠነኛ ነጻነት እየሰጠ እንዲጠብቀውና ወዳጆቹም ገብተው እንዲጠይቁት ፈቃድ እንዲሰጣቸው የመቶ አለቃውን አዘዘው።

24. ከጥቂት ቀን በኋላ፣ ፊልክስ ከአይሁ ዳዊት ሚስቱ ከድሩሲላ ጋር መጣ፤ ጳውሎስንም አስጠርቶ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ማመን ሲናገር አዳመጠው።

25. ጳውሎስ ስለ ጽድቅና ራስን ስለ መግዛት ስለሚመጣውም ፍርድ በሚናገርበት ጊዜ ግን ፊልክስ ፈርቶ፣ “ለጊዜው ይህ ይበቃል፤ ወደ ፊት ሲመቸኝ አስጠራሃለሁ፤ አሁን ልትሄድ ትችላለህ” አለው።

26. ደግሞም ከጳውሎስ ጉቦ ለመቀበል ተስፋ ያደርግ ስለ ነበር፣ በየጊዜው እያስጠራ ያነጋግረው ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 24