ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 24:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ንጹሕ ኅሊና እንዲኖረኝ ሁል ጊዜ እጥራለሁ።

17. “ከብዙ ዓመት በኋላም፣ ለድኻው ወገኔ ምጽዋትና መባ ይዤ ወደ ኢየሩሳሌም መጣሁ።

18. እነርሱም በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዐት ፈጽሜ ይህንኑ ሳደርግ አገኙኝ፤ የሕዝብ ሁካታ ወይም ረብሻ አልነበረም።

19. ነገር ግን ክስ ካላቸው አንተ ፊት ቀርበው ሊከሱ የሚገባቸው ከእስያ አውራጃ የመጡ አንዳንድ አይሁድ አሉ፤

20. ወይም በዚህ ያሉት እነዚህ በሸንጎው ፊት ቀርቤ በነበረበት ጊዜ ያገኙብኝ ወንጀል ካለ ይናገሩ፤

21. በመካከላቸው በቆምሁበት ጊዜ ስለ ሙታን ትንሣኤ ከተናገርሁት አንድ ነገር በስተቀር ዛሬ ተከስሼ የቀረብሁበት ሌላ ነገር የለም።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 24