ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 14:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ከዚያም በየአብያተ ክርስቲያናቱ ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ፣ በጾምና በጸሎት ላመኑበት ጌታ ዐደራ ሰጧቸው።

24. በጲስድያም ዐልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፤

25. በጴርጌንም ቃሉን ከሰበኩ በኋላ፣ ወደ ኢጣልያ ወረዱ።

26. ከአጣልያም፣ እስካሁን ላከናወኑት ሥራ፣ ለእግዚአብሔር ጸጋ በዐደራ ወደ ተሰጡባት ከተማ ወደ አንጾኪያ በመርከብ ተመለሱ።

27. እዚያም በደረሱ ጊዜ፣ ቤተ ክርስቲያንን በአንድነት ሰብስበው፣ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት ያደረገውን ሁሉ፣ ደግሞም ለአሕዛብ እንዴት የእምነትን በር እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።

28. በዚያም ከደቀ መዛሙርት ጋር ብዙ ጊዜ ተቀመጡ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 14