ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሐዋርያት ሥራ 13:35-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

35. ስለዚህ በሌላም ስፍራ፣“ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ ይላል።

36. “ዳዊት በራሱ ዘመን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ካገለገለ በኋላ አንቀላፍቶአል፤ ከአባቶቹም ጋር ተቀብሮ ሥጋው በስብሶአል።

37. እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣው እርሱ ግን መበስበስን አላየም።

38. እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ የኀጢአት ይቅርታ የሚገኘው በኢየሱስ በኩል መሆኑ እንደ ተሰበከላችሁ ዕወቁ፤

39. በእርሱ የሚያምን ሁሉ በሙሴ ሕግ በኩል ማግኘት ያልተቻለውን ጽድቅ ያገኛል።

40. ስለዚህ ነቢያት እንዲህ ብለው የተናገሩት እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሐዋርያት ሥራ 13