ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 8:49-55 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

49. ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ፣ አንድ ሰው ከምኵራብ አለቃው ከኢያኢሮስ ቤት መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች፤ ከዚህ በኋላ መምህሩን አታድክመው” አለው።

50. ኢየሱስም ይህን ሰምቶ ኢያኢሮስን፣ “አይዞህ አትፍራ፤ እመን ብቻ፤ ልጅህ ትድናለች” አለው።

51. ወደ ኢያኢሮስ ቤት ሲገባም ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስና ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና እናት በቀር ማንም አብሮት እንዲገባ አልፈቀደም።

52. በዚህ ጊዜ ሰዎቹ ሁሉ እያለቀሱላት ዋይ ዋይ ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ፤ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው።

53. ሰዎቹም መሞቷን ስላወቁ ሣቁበት።

54. እርሱ ግን እጇን ይዞ፣ “ልጄ ሆይ፤ ተነሺ” አላት።

55. የልጅቷም መንፈስ ተመለሰ፤ ወዲያውም ተነሥታ ቆመች፤ ኢየሱስም የሚበላ ነገር እንዲሰጧት አዘዛቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 8