ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 23:53-56 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

53. በተፈቀደለትም ጊዜ፣ ሥጋውን አውርዶ በበፍታ ገነዘው፤ ከድንጋይ ተፈልፍሎ በተሠራና ገና ማንም ባልተቀበረበት መቃብር ውስጥ አስቀመጠው።

54. ዕለቱ የመዘጋጃ ቀን ነበረ፤ ሰንበትም ሊገባ ነበር።

55. ከገሊላ ጀምሮ ከኢየሱስ ጋር የመጡት ሴቶችም ተከትለው መቃብሩን አዩ፤ ሥጋውንም እንዴት እንዳስቀመጡት ተመለከቱ።

56. ከዚያም ተመልሰው ሽቱና ቅባት አዘጋጁ፤ ሕጉ በሚያዘው መሠረት በሰንበት ቀን ዐረፉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 23