ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 22:63-68 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

63. ኢየሱስን አስረው ይጠብቁት የነበሩት ሰዎችም ያፌዙበትና ይመቱት ጀመር፤

64. ዐይኑንም ሸፍነው፣ “እስቲ ትንቢት ተናገር፤ የመታህ ማነው? እያሉ ይጠይቁት ነበር።

65. ሌላም ብዙ የስድብ ቃል እየተናገሩ ያቃልሉት ነበር።

66. በነጋም ጊዜ፣ የሕዝብ ሽማግሌዎች፣ የካህናት አለቆችና ጸሐፍት ተሰበሰቡ፤ ኢየሱስንም በሸንጎአቸው ፊት አቀረቡት።

67. እነርሱም፣ “አንተ ክርስቶስ ነህን? እስቲ ንገረን” አሉት።ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ብነግራችሁ አታምኑኝም፤

68. ብጠይቃችሁም አትመልሱም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 22