ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 14:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. አንድ ሰንበት ቀን፣ ኢየሱስ ምግብ ሊበላ ከፈሪሳውያን አለቆች አንዱ ወደ ነበረ ሰው ቤት በገባ ጊዜ፣ ሰዎች በዐይን ይከታተሉት ነበር።

2. በዚያም በአካል እብጠት የሚሠቃይ አንድ ሰው ከፊት ለፊቱ ነበር።

3. ኢየሱስም ሕግ ዐዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን፣ “በሰንበት ቀን ሕመምተኞችን መፈወስ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?” ሲል ጠየቃቸው።

4. እነርሱ ግን ዝም አሉ። እርሱም ሰውየውን ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው።

5. ደግሞም፣ “ከእናንተ አንዱ፣ ልጁ ወይም በሬው በሰንበት ቀን ጒድጓድ ቢገባበት ፈጥኖ የማያወጣው ማን ነው?” አላቸው።

6. እነርሱም ለዚህ አንዳች መልስ ሊያገኙ አልቻሉም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 14