ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 1:76-80 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

76. ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፤ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት በፊቱ ትሄዳለህና፤

77. የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣

78. ከአምላካችንም በጎ ምሕረት የተነሣ፣የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤

79. ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”

80. ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም ሕዝብ በይፋ እስከታየበት ቀን ድረስ በበረሓ ኖረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 1