ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 1:70-80 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

70. ይህም ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው፣

71. ማዳኑም ከጠላቶቻችንና፣ከተፃራሪዎቻችን ሁሉ እጅ ነው፤

72. ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣

73. ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማሰብ፣

74. ከጠላቶቻችን እጅ አውጥቶ፣ያለ ፍርሀት እንድናገለግለው፣

75. በዘመናችንም ሁሉ በቅድስናና በጽድቅ በፊቱ ሊያቆመን ነው።

76. ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፤ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት በፊቱ ትሄዳለህና፤

77. የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣

78. ከአምላካችንም በጎ ምሕረት የተነሣ፣የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤

79. ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”

80. ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም ሕዝብ በይፋ እስከታየበት ቀን ድረስ በበረሓ ኖረ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 1