ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሉቃስ 1:55-72 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

55. ይህም ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፣ለአብርሃምና ለዘሩ ያለውን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው።”

56. ማርያምም ሦስት ወር ያህል ኤልሳቤጥ ዘንድ ከቈየች በኋላ ወደ ቤቷ ተመለሰች።

57. የኤልሳቤጥም የመውለጃዋ ቀን ደረሰ፤ ወንድ ልጅም ወለደች።

58. ጎረቤቶቿና ዘመ ዶቿም ጌታ ታላቅ ምሕረት እንዳደረገላት ሰሙ፤ የደስታዋም ተካፋዮች ሆኑ።

59. በስምንተኛውም ቀን ሕፃኑን ሊገርዙት መጡ፤ በአባቱም ስም ዘካርያስ ሊሉት ፈለጉ፤

60. እናቱ ግን፣ “አይሆንም፤ ዮሐንስ መባል አለበት” አለች።

61. እነርሱም፣ “ከዘመዶችሽ በዚህ ስም የተጠራ ማንም የለም” አሏት።

62. አባቱንም ምን ስም ሊያወጣለት እንደሚፈልግ በምልክት ጠየቁት።

63. እርሱም መጻፊያ ሰሌዳ እንዲሰጡት ለምኖ፣ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ፤ ሁሉም በነገሩ ተደነቁ።

64. ወዲያውም አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱ ተፈታ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ መናገር ጀመረ።

65. ጎረቤቶቹም ሁሉ በፍርሀት ተሞሉ፤ ይህም ሁሉ ነገር በደጋማው የይሁዳ ምድር ሁሉ ተወራ።

66. ይህንም የሰሙ ሁሉ፣ “ይህ ሕፃን ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ያዙ፤ የጌታ እጅ በርግጥ ከእርሱ ጋር ነበርና።

67. የሕፃኑም አባት ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል ትንቢት ተናገረ፤

68. “የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቶአልና።

69. በባሪያው በዳዊት ቤት፣የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፤

70. ይህም ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው፣

71. ማዳኑም ከጠላቶቻችንና፣ከተፃራሪዎቻችን ሁሉ እጅ ነው፤

72. ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሉቃስ 1