ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

3 ዮሐንስ 1:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሽማግሌው፤በእውነት ለምወደው ለውድ ወዳጄ፣ ለጋይዮስ፤

2. ወዳጅ ሆይ፤ ነፍስህ በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለች ሁሉ መልካም ጤንነት እንዲኖርህና በነገር ሁሉ እንዲሳካልህ እጸልያለሁ።

3. ለእውነት ታማኝ እንደሆንህና የምትመላለሰውም በእውነት እንደሆነ አንዳንድ ወንድሞች መጥተው ስለ አንተ ሲመሰክሩልኝ እጅግ ደስ አለኝ።

4. ልጆቼ በእውነት የሚመላለሱ መሆናቸውን ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም።

5. ወዳጅ ሆይ፤ ለአንተ እንግዶች ቢሆኑም እንኳ ለወንድሞች በምታደርገው ነገር ሁሉ ታማኝ ነህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 3 ዮሐንስ 1