ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ጴጥሮስ 3:4-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. እነርሱም፣ “ ‘እመጣለሁ’ ያለው ታዲያ የት አለ? አባቶች ከሞቱበት ከፍጥረት መጀመሪያ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል” ይላሉ።

5. ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ሰማያት ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው እንደሚኖሩ፣ መሬትም በውሃ መካከልና በውሃም እንደ ተሠራች ሆን ብለው ይክዳሉ፤

6. በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ጴጥሮስ 3