ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ተሰሎንቄ 2:12-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ይህም የሚሆነው እውነትን ያላመኑት ነገር ግን በክፋት ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ እንዲፈረድባቸው ነው።

13. በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፤ እኛ ግን ሁል ጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ይገባናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር እናንተን ከመጀመሪያ አንሥቶ በመንፈስ ተቀድሳችሁና በእውነትም አምናችሁ እንድትድኑ መርጦአችኋል።

14. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ተካፋዮች እንድ ትሆኑም በወንጌላችን አማካይነት ጠርቶአችኋል።

15. እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በአንደበታችንም ሆነ በመልእክታችን ያስተላለፍንላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ።

16. ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞም እኛን የወደደንና በጸጋው የዘላለም መጽናናትና መልካም ተስፋን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣

17. ልባችሁን ያጽናኑት፤ በበጎ ሥራና በቃል ሁሉ ያበርቷችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ተሰሎንቄ 2