ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ቆሮንቶስ 7:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ወደ ድነት ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም። ዓለማዊ ሐዘን ግን ለሞት ያበቃል።

11. ይህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነው ሐዘን እንዴት ያለ ትጋት፣ እንዴት ያለ መልስ የመስጠት ችሎታ፣ እንዴት ያለ ቍጣ፣ እንዴት ያለ ፍርሀት፣ እንዴት ያለ ናፍቆት፣ እንዴት ያለ በጎ ቅናት፣ እንዴት ያለ ተግሣጽ እንዳ ስገኘላችሁ ተመልከቱ። በዚህም ጒዳይ ንጹሓን መሆናችሁን በሁሉ ረገድ አስመስክራችኋል።

12. እንግዲህ እኔ የጻፍሁላችሁ ስለ በደለው ወይም ስለ ተበደለው ሰው አይደለም፤ ነገር ግን ለእኛ ምን ያህል ታማኞች እንደሆናችሁ፣ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን እንድታዩ በማለት ነው።

13. እኛም የተጽናናነው በዚህ ምክንያት ነው።ከእኛም መጽናናት በተጨማሪ በቲቶ ደስታ እኛም ይበልጥ ደስ ብሎናል፤ ምክንያቱም ሁላችሁም መንፈሱን አሳርፋችኋል።

14. በእናንተ ላይ ያለኝን ትምክሕት ለእርሱ ነግሬው ነበር፤ እናንተም አላሳፈራችሁኝም። ነገር ግን ስንነግራችሁ የነበረው ሁሉ እውነት እንደሆነ፣ እንደዚሁም ስለ እናንተ ለቲቶ በትምክሕት የነገርነው እውነት መሆኑ ተረጋግጦአል።

15. እርሱም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ እንዴት እንደ ተቀበላችሁትና ሁላችሁም እንደ ታዘዛችሁ ሲያስታውስ ለእናንተ ያለው ፍቅር እየበረታ ሄዶአል።

16. እኔም በማናቸውም ነገር ልተማመንባችሁ በመቻሌ ደስ ብሎኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ቆሮንቶስ 7