ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ቆሮንቶስ 6:15-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ክርስቶስ ከቤልሆር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ኅብረት አለው?

16. የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሮአል፤ “ከእነርሱ ጋር እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”

17. “ስለዚህ ከመካከላቸው ውጡ፤ለእኔም የተለያችሁ ሁኑ፤ይላል ጌታ።ርኩስ የሆነውን ነገር አትንኩ፤እኔም እቀበላችኋለሁ።”

18. “እኔ አባት እሆናችኋለሁ፤እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼትሆናላችሁ፤ይላል ሁሉን የሚችል ጌታ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ቆሮንቶስ 6