ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ቆሮንቶስ 6:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን መጠን፣ የተቀበላችሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ከንቱ እንዳታደርጉት ዐደራ እንላችኋለን።

2. እርሱ፣“በትክክለኛው ሰዓት ሰማሁህ፤በመዳንም ቀን ረዳሁህ” ይላልና።እነሆ፤ ትክክለኛው ሰዓት አሁን ነው፤የመዳንም ቀን አሁን ነው።

3. አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ፣ ለማንም ዕንቅፋት መሆን አንፈልግም።

4. ይሁን እንጂ በምናደርገው ነገር ሁሉ ራሳችንን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች እናቀርባለን፦ በብዙ ትዕግሥት፣ በመከራ፣ በችግር፣ በጭንቀት፣

5. በመገረፍ፣ በመታሰር፣ በሁከት፣ በሥራ ብዛት፣ እንቅልፍ በማጣት፣ በመራብ፣

6. በንጽሕና፣ በዕውቀት፣ በትዕግሥት፣ በቸርነት፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በእውነተኛ ፍቅር፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ቆሮንቶስ 6